“የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ሁሉም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱም፥ እንደሚያንቀላፉ፥ እንደሚጋደሙ፥ እንደሚያልሙና መጮኽ እንደማይችሉ ውሾች ናቸው።
1 ጢሞቴዎስ 3:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አንድ ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ነቀፋ የሌለበት፥ አንዲት ሚስት ብቻ ያገባ፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚገዛ፥ በሥርዓት የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ችሎታ ያለው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልከኛ፣ ራሱን የሚገዛ፣ በሥርዐት የሚኖር፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ማስተማር የሚችል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ በሥርዓት የሚሠራ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ |
“የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ሁሉም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱም፥ እንደሚያንቀላፉ፥ እንደሚጋደሙ፥ እንደሚያልሙና መጮኽ እንደማይችሉ ውሾች ናቸው።
እንዲሁም በዚያን ጊዜ ከአሴር ነገድ የሆነች የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች። በዕድሜዋም በጣም የገፋች ሴት ነበረች፤ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ከተቀመጠች በኋላ ባልዋ ሞተባት፤
ይህም ከሆነ በዚህ በጠማማና በመጥፎ ትውልድ መካከል ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ንጹሓን የእግዚአብሔር ልጆች በመሆን በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት ታበራላችሁ።
እንደእነዚህ ያሉት ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎችም እርሱን እያመሰገኑ እንዲመገቡት እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን ምግብ “አትብሉ” እያሉ ይከለክላሉ።
እንዲሁም ልጆችን በሚገባ በማሳደግ፥ እንግዳን በመቀበል፥ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፥ የተቸገሩትን በመርዳትና ማንኛውንም በጎ ሥራ ሁሉ በማከናወን ለመልካም ሥራም ሁሉ የተጋች መሆን አለባት።
እንግዳ ተቀብሎ ማስተናገድን አትርሱ፤ እንደዚህ እንግዶችን እየተቀበሉ በማስተናገድ አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ መላእክትን ተቀብለው አስተናግደዋል።