የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ለአገልጋይህ ቤት እሠራለሁ ብለህ ስለ ገለጥክለት አገልጋይህ ይህን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።
1 ሳሙኤል 9:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል እንዲህ ብሎ ገልጦለት ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል ይህን እንዲህ ሲል ገልጾለት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት ጌታ ለሳሙኤል እንዲህ ሲል ገልጦለት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገናም ሳኦል ሳይመጣ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል ጆሮውን ከፈተለት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገናም ሳኦል ሳይመጣ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ ብሎ ገልጦለት ነበር፦ |
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ለአገልጋይህ ቤት እሠራለሁ ብለህ ስለ ገለጥክለት አገልጋይህ ይህን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።
“ከዚያም ቀጥሎ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው እግዚአብሔርን ለመኑ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለአርባ ዓመት አነገሠላቸው።
ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ እግዚአብሔር የላከኝ እኔ ነኝ፤ አሁንም ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር የሚለውን ስማ፤
ዮናታንም “ይህንንስ ከአንተ ያርቀው! አትሞትም፤ ትልቅም ሆነ ትንሽ አባቴ ከእኔ የሚሰውረው ነገር የለም፤ ይህንንም ነገር ቢሆን አባቴ ከእኔ አይሰውርም በፍጹም አይደረግም!” አለው።
ከዚያም በኋላ ሳኦልና አገልጋዩ ወደ ከተማይቱ ወጡ፤ ወደ ከተማይቱም በመግባት ላይ ሳሉ ሳሙኤል ወደ ማምለኪያው ስፍራ ለማለፍ ወደ እነርሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት።