እኔ እነርሱን ከነዚህ ከፍተኛ አለቶች ላይ ሆኜ አያቸዋለሁ፤ ከኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከታቸዋለሁ፤ እነርሱ ለብቻቸው የሚኖሩ ሕዝብ ናቸው። እነርሱ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የተለዩ መሆናቸውን ያውቃሉ።
1 ሳሙኤል 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ! አንተ በእርጅና ላይ ነህ፤ ልጆችህም የአንተን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ስለዚህ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው እኛን የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህ ያንተን ፈለግ አይከተሉም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ አሁንም እንደ ሌሎች አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፥ አሁንም እንደ አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አድርግልን አሉት። |
እኔ እነርሱን ከነዚህ ከፍተኛ አለቶች ላይ ሆኜ አያቸዋለሁ፤ ከኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከታቸዋለሁ፤ እነርሱ ለብቻቸው የሚኖሩ ሕዝብ ናቸው። እነርሱ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የተለዩ መሆናቸውን ያውቃሉ።
“ከዚያም ቀጥሎ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው እግዚአብሔርን ለመኑ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለአርባ ዓመት አነገሠላቸው።
ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ጌዴዎንን “አንተ ከምድያማውያን እጅ አድነኸናልና አንተና ከአንተም በኋላ ልጆችህ እንዲሁም የልጅ ልጆችህ ገዢዎቻችን ሁኑ፤” አሉት።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ያዳናችሁን አምላካችሁን ትታችኋል፤ እናንተም፦ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አላችሁት። ስለዚህ አሁን በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ”።
እነሆ አሁን እንደምታውቁት የፀሐይ ሙቀት የበዛበት የስንዴ መከር ወራት አይደለምን? ነገር ግን እኔ አሁን እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና ዝናብ ይልካል፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ንጉሥ እንዲያነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ ምክንያት በደል በመሥራት እግዚአብሔርን ያሳዘናችሁ መሆናችሁን ታረጋግጣላችሁ።”
ከእንግዲህ ወዲህ የሚመራችሁ ንጉሥ አግኝቼአለሁ፤ እኔ ግን ዕድሜዬ ስለ ገፋ ሸምግዬአለሁ፤ ልጆቼም ከእናንተው ጋር አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የእናንተ መሪ ሆኜ ቈይቼአለሁ።
ከሦስት ቀን በፊት የጠፉት አህዮችህ ተገኝተዋልና ስለ እነርሱ አትጨነቅ፤ ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ምኞት ማንን ለማግኘት ይመስልሃል? እነርሱ የሚፈልጉት አንተንና የአባትህን ቤተሰብ አይደለምን?” አለው።