ዳዊትም “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው። እርሱም “ሠራዊታችን ከጦር ግንባር ሸሸ፤ ከሰዎቻችንም ብዙዎቹ ሞቱ፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።
1 ሳሙኤል 4:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም ቀርቦ “እኔ ከጦርነቱ አምልጬ መጣሁ፤ ዛሬም እዚህ የደረስኩት በብርቱ ሩጫ ነው” አለ። ዔሊም “ልጄ ሆይ! ታዲያ እንዴት ሆነ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም ዔሊን፣ “ከጦሩ ሜዳ ገና አሁን መምጣቴ ነው፤ ከጦርነቱ አምልጬ የወጣሁትም ዛሬውኑ ነው” ብሎ ነገረው። ዔሊም፣ “ልጄ ሆይ፤ ታዲያ እንዴት ሆነ?” ሲል ጠየቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውየውም ዔሊን፥ “ከጦሩ ሜዳ ገና አሁን መምጣቴ ነው፤ ከጦርነቱ አምልጬ የወጣሁትም ዛሬውኑ ነው” ብሎ ነገረው። ዔሊም፥ “ልጄ ሆይ፤ ታዲያ እንዴት ሆነ?” ሲል ጠየቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውዬውንም፥ “አንተ ከወዴት ነህ?” አለው። እርሱም፥ “ጦርነቱ ከአለበት ስፍራ የመጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰልፍ ሸሸሁ” አለ። እርሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገሩስ እንዴት ሆነ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ዔሊን፦ ከሰልፍ የመጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰልፍ ኮበለልሁ አለ። እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ ነገሩሳ እንዴት ሆነ? አለው። |
ዳዊትም “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው። እርሱም “ሠራዊታችን ከጦር ግንባር ሸሸ፤ ከሰዎቻችንም ብዙዎቹ ሞቱ፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።
እግዚአብሔር እንደገና ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለ ጠራኸኝ መጥቼአለሁ” አለው፤ ዔሊ ግን “ልጄ ሆይ! እኔ አልጠራሁህም፤ ወደ መኝታህ ተመልሰህ ተኛ” አለው።
ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።