ዮሴፍ የእናቱ ልጅ የሆነውን ወንድሙን ብንያምን ባየው ጊዜ “ ‘ታናሽ ወንድም አለን’ ብላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ይህ እርሱ ነውን?” አለና “ልጄ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።
1 ሳሙኤል 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንደገና ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለ ጠራኸኝ መጥቼአለሁ” አለው፤ ዔሊ ግን “ልጄ ሆይ! እኔ አልጠራሁህም፤ ወደ መኝታህ ተመልሰህ ተኛ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እግዚአብሔር፣ “ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሣና ወደ ዔሊ ሄዶ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊም መልሶ፣ “ልጄ ሆይ፤ እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም እግዚአብሔር፥ “ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሣና ወደ ዔሊ ሄዶ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም ግን፥ “ልጄ ሆይ፤ እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ደግሞ፥ “ሳሙኤል! ሳሙኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሥቶ ዳግመኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። እርሱም፥ “አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ሳሙኤል ሆይ ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፦ እነሆኝ የጠራኸኝ አለ። |
ዮሴፍ የእናቱ ልጅ የሆነውን ወንድሙን ብንያምን ባየው ጊዜ “ ‘ታናሽ ወንድም አለን’ ብላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ይህ እርሱ ነውን?” አለና “ልጄ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።
አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው።
በዚያም ሰዎች በአልጋ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ይዘው ወደ እርሱ መጡ። እርሱም እምነታቸውን አይቶ፥ ሽባውን፥ “ልጄ ሆይ! አይዞህ፤ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።
ወደ ዔሊ ዘንድ ሮጦ በመሄድ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለ። ዔሊ ግን “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ሂድና ተኛ” አለው፤ ሳሙኤልም ተመልሶ ተኛ።
ሰውየውም ቀርቦ “እኔ ከጦርነቱ አምልጬ መጣሁ፤ ዛሬም እዚህ የደረስኩት በብርቱ ሩጫ ነው” አለ። ዔሊም “ልጄ ሆይ! ታዲያ እንዴት ሆነ?” አለው።