ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል።
1 ሳሙኤል 26:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳዊት ከሸለቆው ባሻገር ወደሚገኘው ቦታ ተሻገረ፤ ከእነርሱም ራቅ ብሎ በተራራው ጫፍ ላይ ቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዳዊት ወደ ማዶ ተሻግሮ በኰረብታው ጫፍ ላይ ራቅ ብሎ ቆመ፤ በመካከላቸውም ሰፊ ርቀት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዳዊት ወደ ማዶ ተሻግሮ በኰረብታው ጫፍ ላይ ራቅ ብሎ ቆመ፤ በመካከላቸውም ሰፊ ርቀት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ማዶ ተሻገረ፤ በተራራውም ራስ ላይ ርቆ ቆመ፤ በመካከላቸውም ሰፊ ርቀት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደዚያ ተሻገረ፥ በተራራውም ራስ ላይ ርቆ ቆመ፥ በመካከላቸውም ሰፊ ስፍራ ነበረ። |
ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል።
ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ ሳኦልን በመከተል “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” አለው፤ ሳኦልም መለስ ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊት በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣውና እንዲህ አለው፤
ስለዚህም ዳዊት ጦሩንና ውሃ መቅጃውን ከሳኦል ራስጌ አንሥቶ እርሱና አቢሳ ከዚያ ሄዱ፤ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከባድ እንቅልፍ ልኮባቸው ተጫጭኖአቸው ተኝተው ስለ ነበር ይህ ሁሉ ሲሆን ማንም ነቅቶ ያየና ያወቀ አልነበረም።
ድምፁንም ከፍ አድርጎ ወደ ሳኦል ወታደሮችና ወደ አበኔር በመጮኽ “አበኔር ሆይ! መልስ ስጠኝ” አለው። አበኔርም “እንዲህ እያልክ በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” አለ።