1 ሳሙኤል 25:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዮቹም እርስዋ ወዳለችበት ወደ ቀርሜሎስ ሄደው “ሊያገባሽ ስለ ፈቀደ ወደ ዳዊት ልንወስድሽ መጥተናል” አሉአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዮቹም ወደ ቀርሜሎስ ሄደው አቢግያን፣ “ሚስት ትሆኚው ዘንድ እንድንወስድሽ ዳዊት ወደ አንቺ ልኮናል” አሏት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዮቹም ወደ ቀርሜሎስ ሄደው አቢጌልን፥ “ሚስት ትሆኚው ዘንድ እንድንወስድሽ ዳዊት ወደ አንቺ ልኮናል” አሏት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ብላቴኖች ወደ ቀርሜሎስ ወደ አቤግያ መጡ፥ “ዳዊትም ሚስት ትሆኚው ዘንድ ወደ አንቺ ልኮናል” ብለው ነገሩአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ባሪያዎች ወደ ቀርሜሎስ ወደ አቢግያ በመጡ ጊዜ፦ ዳዊት ያገባሽ ዘንድ ወደ አንቺ ልኮናል ብለው ነገሩአት። |
ሞገስ ያላት ሴት ትከበራለች፤ መልካም ጠባይ የሌላት ሴት ግን ውርደት ያገኛታል። ሰነፍ ሰው ሀብት ማግኘት አይችልም፤ ታታሪ ሰው ግን ሀብታም ይሆናል።
ዳዊትም የናባልን መሞት በሰማ ጊዜ “እኔን በመስደቡ እግዚአብሔር ናባልን ስለ ተበቀለውና እኔንም ከስሕተት ስለ ጠበቀኝ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ ናባልን ስለ ክፉ ሥራው ቀጥቶታል” አለ። ከዚህም በኋላ ዳዊት ወደ አቢጌል መልእክተኛ ልኮ ሊያገባት መፈለጉን ገለጠላት።