እነዚህንም በየመንጋው ከፈለና ለእያንዳንዳቸው እረኞች መደበላቸው፤ እረኞቹንም “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፤ በየመንጋው መካከል ርቀት እንዲኖር አድርጋችሁ፥ በመከታተል ሂዱ” አላቸው።
1 ሳሙኤል 25:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ አገልጋዮቹን “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋላሁ” አለቻቸው፤ ለባልዋ ግን የነገረችው ቃል አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አገልጋዮቿን፣ “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋለሁ” አለቻቸው፤ ለባሏ ለናባል ግን አልነገረችውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አገልጋዮቹን፥ “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋለሁ” አለቻቸው፤ ለባሏ ለናባል ግን አልነገረችውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአገልጋዮችዋም፥ “አስቀድማችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነሆም እከተላችኋለሁ” አለች። ይህንም ለባልዋ ለናባል አልነገረችውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለብላቴኖችዋም፦ አስቀድማችሁ በፊቴ ሂዱ፥ እነሆም፥ እከተላችኋለሁ አለች። ይህንም ለባልዋ ለናባል አልነገረችውም። |
እነዚህንም በየመንጋው ከፈለና ለእያንዳንዳቸው እረኞች መደበላቸው፤ እረኞቹንም “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፤ በየመንጋው መካከል ርቀት እንዲኖር አድርጋችሁ፥ በመከታተል ሂዱ” አላቸው።
‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው።
አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን የጦር መሣሪያ የሚሸከምለትን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ነገር ግን ዮናታን ይህን ጉዳይ ለአባቱ እንኳ አልነገረውም፤
እርስዋም በአህያ ላይ ተቀምጣ እየጋለበች በኮረብታው ጥግ በሚገኘው ጠመዝማዛ መንገድ ስትወርድ በድንገት ዳዊትና ተከታዮቹ ወደ እርስዋ ሲመጡ አገኘቻቸው፤
አቢጌልም እንደ ቤተ መንግሥት ግብር ታላቅ ግብዣ በማድረግ ላይ ወደነበረው ወደ ናባል ተመልሳ ሄደች፤ እርሱም ሰክሮ በደስታ ይፈነድቅ ስለ ነበር እስከ ማግስቱ ጧት ድረስ ምንም ቃል አልነገረችውም፤