እግዚአብሔር ይህን ምልክት ይሰጣል፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱ ላይ ያለውም ዐመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካይነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይህ እንደ ተፈጸመ ወዲያውኑ ትገነዘባለህ’ ” አለ።
1 ሳሙኤል 2:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሁለቱ ልጆችህ የሖፍኒና የፊንሐስ ዕድል ፈንታ ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ በሁለቱ ልጆችህ በሖፍኒና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፤ ሁለቱ በአንድ ቀን በጦር ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፥ ሁለቱ በአንድ ቀን ይሞታሉ። |
እግዚአብሔር ይህን ምልክት ይሰጣል፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱ ላይ ያለውም ዐመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካይነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይህ እንደ ተፈጸመ ወዲያውኑ ትገነዘባለህ’ ” አለ።
አኪያም የሚናገረውን የትንቢት ቃል በመቀጠል ለኢዮርብዓም ሚስት እንዲህ አላት፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ቤትሽ ተመልሰሽ ሂጂ፤ ወደ ከተማም እንደ ገባሽ ወዲያውኑ ልጁ ይሞታል፤
በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በወጣትነት ዕድሜአቸው በሰይፍ ያልቃሉ፤
በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤
ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።