እነርሱም “አንተ ከእኛ ጋር መሄድ የለብህም፤ ጥቂቶቻችን ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ ወይም ግማሾቻችን ብንገደል ጠላት ምንም አይገደውም፤ አንተ ግን ከእኛ ዐሥሩን ሺህ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ አንተ እዚሁ በከተማይቱ ውስጥ ቈይተህ አስፈላጊውን ርዳታ ብትልክልን ይሻላል” አሉት።
1 ሳሙኤል 18:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶቹም ባደረጉት የአቀባበል ሥርዓት ላይ “ሳኦል ሺህ ገዳይ! ዳዊት ግን ዐሥር ሺህ ገዳይ!” እያሉ ዘፈኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቶቹም እንዲህ ሲሉ በመቀባበል ዘፈኑ፤ “ሳኦል ሺሕ ገደለ፤ ዳዊት ግን ዐሥር ሺሕ ገደለ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶችም “ሳኦል ሺ ገዳይ! ዳዊት ዐሥር ሺ ገዳይ!” እያሉ በቅብብል ይዘፍኑ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶችም፥ “ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊትም ዐሥር ሺህ ገደለ” እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቶችም፦ ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር። |
እነርሱም “አንተ ከእኛ ጋር መሄድ የለብህም፤ ጥቂቶቻችን ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ ወይም ግማሾቻችን ብንገደል ጠላት ምንም አይገደውም፤ አንተ ግን ከእኛ ዐሥሩን ሺህ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ አንተ እዚሁ በከተማይቱ ውስጥ ቈይተህ አስፈላጊውን ርዳታ ብትልክልን ይሻላል” አሉት።
እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤልም ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው።
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ የበገና፥ የመሰንቆ፥ የከበሮ፥ የጸናጽልና የቃጭል ድምፅ እያሰሙ ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።
የንጉሡ ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖች “ይህ በአገሩ የነገሠው ዳዊት አይደለምን? ‘ሳኦል ሺህ ገዳይ! ዳዊት ዐሥር ሺህ ገዳይ!’ እያሉ ሴቶች በጭፍራ የዘፈኑለት እርሱ አይደለምን?” ሲሉ አኪሽን ጠየቁት።