ከአሁን በፊት ሳኦል የእኛ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንኳ በጦርነት እስራኤልን የምትመራ አንተ ነበርክ፤ እንዲሁም ሕዝቡን እስራኤልን እንድትመራና በእስራኤልም ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶልሃል።”
1 ሳሙኤል 18:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ተልእኮው የሚሳካለት መሪ በመሆኑ በእስራኤልም ሆነ በይሁዳ የሚገኝ ሕዝብ ሁሉ ዳዊትን ይወድ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን ዳዊትን ወደዱት፤ በፊታቸው እየወጣና እየገባ የሚመራቸው እርሱ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን በፊታቸው እየወጣና እየገባ የሚመራቸው እርሱ ነበርና ዳዊትን ወደዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለ ነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱ። |
ከአሁን በፊት ሳኦል የእኛ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንኳ በጦርነት እስራኤልን የምትመራ አንተ ነበርክ፤ እንዲሁም ሕዝቡን እስራኤልን እንድትመራና በእስራኤልም ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶልሃል።”
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ደረጃ ከንጉሥ አርጤክስስ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበር፤ እርሱም በወገኖቹ በአይሁድ ዘንድ በጣም የተከበረና የተወደደ ሰው ነበር፤ መርዶክዮስ ለወገኖቹና ለዘሮቻቸው በሰላም የመኖር ዋስትና ለማስገኘት በብርቱ የደከመ ሰው ነበር።
የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ ዐውቀው በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።
ሳኦል በትእዛዝ በሚያዘምትበት ቦታ ሁሉ የዳዊት ተልእኮ የተሳካ ሆነ፤ ስለዚህም ሳኦል በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የመኰንንነት ማዕርግ እንዲኖረው አደረገ፤ ይህም የሳኦልን የጦር መኰንኖችና ወታደሮችን ሁሉ አስደሰተ።