1 ሳሙኤል 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮቹም ከነሐስ በተሠራ ገንባሌ የተሸፈኑ ነበሩ፤ ከነሐስ የተሠራ ጦርም በትከሻው ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግሮቹ ላይ የናስ ገምባሌ አድርጎ፣ በጫንቃው ላይ ደግሞ የናስ ጭሬ ይዞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግሮቹም ላይ የሐናስ ገምባሌ አድርጎ፥ በጫንቃው ላይ ደግሞ የናሐስ ጭሬ ይዞ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግሮቹም ላይ የናስ ገምባሌ ነበረ፤ የናስም ጭሬ በትከሻው ላይ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግሮቹም ላይ የናስ ገምባሌ ነበረ፥ የናስም ጭሬ በትከሻው ላይ ነበረ። |
ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ “አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ሾተል ይዘህ መጥተህብኛል፤ እኔ ደግሞ አንተ በምትፈታተነውና በእስራኤል ሠራዊት አምላክ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ፤