ሳኦልም ዳዊትን፦ “አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እርሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ስለ ሆነ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው።
1 ሳሙኤል 17:56 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም “ሄደህ ይህ ወጣት የማን ልጅ እንደ ሆነ አጥንተህ ዕወቅ” ሲል አዘዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “እንግዲህ ወጣቱ የማን ልጅ እንደ ሆነ ተከታትለህ ድረስበት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “እንግዲህ ወጣቱ የማን ልጅ እንደሆነ ተከታትለህ ድረስበት” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ይህ ብላቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይቅና ዕወቅ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ ይህ ብላቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይቅ አለ። |
ሳኦልም ዳዊትን፦ “አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እርሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ስለ ሆነ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው።
ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው።
ስለዚህ ዳዊት ጎልያድን ገድሎ ወደ ጦር ሰፈር በተመለሰ ጊዜ አበኔር ተቀብሎ ወደ ሳኦል አቀረበው፤ በዚህን ጊዜ ዳዊት የጎልያድን ራስ እንደ ያዘ ነበር፤