1 ሳሙኤል 15:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ ጤሌም በሚባል ስፍራ ቈጠራቸው፤ የወታደሮቹም ብዛት ከእስራኤል ሁለት መቶ ሺህ ከይሁዳ ዐሥር ሺህ ሆነው ተገኙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሳኦል ሰዎቹን ጥላኢም በተባለ ቦታ ሰብስቦ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺሕ እግረኛ ወታደሮችና ከይሁዳም ዐሥር ሺሕ ሰዎች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሳኦል ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ ጤሌም በሚባል ስፍራ ቆጠራቸው፤ የእግረኛ ወታደሮቹ ብዛት ሁለት መቶ ሺህና ከይሁዳ ዐሥር ሺህ ሰዎች ሆነው ተገኙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ሕዝቡን ጠርቶ በጌልጌላ ቈጠራቸው፤ አራት መቶ ሺህ እግረኞች፥ ከይሁዳም ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ሕዝቡን ጠርቶ በጌልገላ ቆጠራቸው፥ ሁለት መቶ ሺህ እግረኞች፥ ከይሁዳም አሥር ሺህ ሰዎች ነበሩ። |
ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ ሄደ፤ ሳኦልም ከወታደሮቹ ጋር ለመደባለቅ ሲሄድ የቀሩት ሰዎች ተከተሉት፤ ከጌልገላም ተነሥተው በብንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ሄዱ፤ ሳኦልም ሠራዊቱን በቈጠረ ጊዜ ብዛታቸው ስድስት መቶ ሆኖ ተገኘ፤