1 ሳሙኤል 14:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጀግንነትም ተዋግቶ የዐማሌቅን ሕዝብ እንኳ ሳይቀር ድል መታ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው እጅ አዳነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጀግንነት ተዋግቶ አማሌቃውያንን አሸነፈ፤ እስራኤልንም ይዘርፏቸው ከነበሩት እጅ ታደጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጀግንነት ተዋግቶ አማሌቃውያንን አሸነፈ፤ እስራኤልንም ይዘርፏቸው ከነበሩት እጅ ታደጋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ጀግና ነበረ፤ አማሌቃውያንንም መታ፤ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ጀግና ነበረ፥ አማሌቃውያንንም መታ፥ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።
ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክህ ምድሪቱን አውርሶህ በዙሪያህ ከሚኖሩ ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ በምድር ላይ ማንም የሚያስታውሳቸው እስኪጠፋ ድረስ ዐማሌቃውያንን ሁሉ ደምስስ! ይህን ከቶ አትርሳ!