Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 17:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እስራኤላውያን በረፊዲም ሳሉ ዐማሌቃውያን መጥተው አደጋ ጣሉባቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አማሌቃውያን መጥተው እስራኤላውያንን ራፊዲም ላይ ወጉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አማሌቅም መጥቶ በረፊድም ከእስራኤል ጋር ተዋጋ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዐማ​ሌ​ቅም መጥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋራ በራ​ፊድ ተዋጋ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 17:8
13 Referencias Cruzadas  

እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ እየተቃወሙ አስቸግረዋቸው ስለ ነበረ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ለመቅጣት ወስኖአል።


የዔሳው ልጅ ኤሊፋዝ ቲመናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርስዋ ለኤሊፋዝ ዐማሌቅን ወለደችለት፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች ናቸው።


ዳዊትና ተከታዮቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ ሲደርሱ ዐማሌቃውያን ኔጌብንና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ በጺቅላግም ላይ አደጋ ጥለው አቃጠሉአት።


ከዚህ በኋላ በለዓም ወደ ዐማሌቅ በመመልከት እንዲህ ሲል ይህን የትንቢት ቃል ተናገረ፦ “ዐማሌቅ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል ሕዝብ ነበረ፤ በመጨረሻ ግን እርሱ ራሱ ለዘለዓለም ይጠፋል።”


የጌባል፥ የዐሞን፥ የዐማሌቅ፥ የፍልስጥኤምና የጢሮስ ሰዎች ናቸው።


ቆሬ፥ ገዕታምና ዐማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም የኤልፋዝ ነገድ አለቆች ሲሆኑ፥ እነርሱም ዔሳው ከሚስቱ ከዓዳ የወለዳቸው ናቸው።


መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም።


በዚያን ጊዜ ውስጥ ዳዊትና ተከታዮቹ በጌሪሹራውያን፥ በጌዛውያንና በአማሌቃውያን ላይ ዘመቱ፤ እነዚህም አገሮች ከቴሌኦም ጀምሮ ወደ ሱርና ወደ ምድረ ግብጽ የሚወስዱ እነርሱ የሚኖሩባቸው አገሮች ነበሩ።


ከዚያም ተመልሰው ወደ ቃዴስ መጡ፤ በዚያን ጊዜ የዚህ ቦታ ስም ዔይንሚሽፖጥ ይባል ነበር። የዐማሌቃውያንንም ምድር ሁሉ ያዙ፤ በሐጸጾን ታማር ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንንም አሸነፉ።


ዐማሌቃውያን በኔጌብ ምድር የሚኖሩ ሲሆን፥ ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በተራራማው አገር፥ ከነዓናውያን ደግሞ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርና በሜዲቴራኒያን በባሕር ዳር ይኖራሉ።”


እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ምድያማውያን፥ ከዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች እየመጡ አደጋ ይጥሉባቸው ነበር።


በጀግንነትም ተዋግቶ የዐማሌቅን ሕዝብ እንኳ ሳይቀር ድል መታ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው እጅ አዳነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios