1 ሳሙኤል 14:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ ዛሬ ሕዝባችን ጠላትን ድል መትቶ ከምርኮ የሚያገኘውን ምግብ ቢመገብ ኖሮ እንዴት በተሻለው ነበር? የሚገድሉአቸው ፍልስጥኤማውያን ቊጥር ምን ያኽል ይበዛ እንደ ነበር እስቲ ገምት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው እጅ ከወሰዱት ምርኮ ዛሬ በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር፤ የተገደሉትም ፍልስጥኤማውያን ቍጥር ከዚህ በበለጠ ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው እጅ ከወሰዱት ምርኮ ዛሬ በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር፤ የተገደሉትም ፍልስጥኤማውያን ቍጥር ከዚህ በበለጠ ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይልቅስ ሕዝቡ ካገኙት ከጠላቶቻቸው ምርኮ በልተው ቢሆን ኑሮ የፍልስጥኤማውያን መመታት ይበልጥ አልነበረምን?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይልቅስ ሕዝቡ ካገኙት ከጠላቶቻቸው ምርኮ በልተው ቢሆኑ የፍልስጥኤማውያን መመታት ይበልጥ አልነበረምን? አለ። |
ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አባቴ በሕዝባችን ላይ የፈጠረው ችግር ምን ያኽል ከባድ ነው! ትንሽ ማር. አግኝቼ በመብላት ብርታት አግኝቼ ዐይኔ እንደ በራ ተመልከት!
በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከሚክማስ እስከ አያሎን ባለው መንገድ ሁሉ እያሳደዱ በመውጋት ፍልስጥኤማውያንን ድል መቱ፤ በዚህም ጊዜ እስራኤላውያንም በራብ እጅግ ዝለው ነበር።