ምናልባት አሁን እንኳ በዋሻ ውስጥ ወይም በሌላ ስፍራ ተሸሽጎ ሊሆን ይችላል፤ ዳዊት በአንተ ሠራዊት ላይ አደጋ እንደ ጣለባቸው የሚሰማ ሰው ሁሉ ወዲያውኑ ወታደሮችህ እንደ ተሸነፉ አድርጎ ያወራል።
1 ሳሙኤል 14:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያውም ግድያ በአንድ የእርሻ ክልል ላይ ኻያ ያኽል ሰዎችን ገደሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በመጀመሪያው ቀን ባደረጉት ግዳይ አንድ ጥማድ በምታውል የዕርሻ ቦታ ላይ ሃያ ያህል ሰዎች ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በመጀመሪያው ቀን ባደረጉት ግዳያቸው በአንድ ጥማድ የእርሻ ቦታ ላይ ሃያ ያህል ሰዎች ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮናታንና የጋሻ ጃግሬውም በወንጭፍና በዱላ የመጀመሪያ ግድያቸው በአንድ ትልም እርሻ መካከል ሃያ ያህል ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮናታንና የጋሻ ጃግሬውም የመጀመሪያ ግዳያቸው በአንድ ትልም እርሻ መካከል ሀያ ያህል ሰው ነበረ። |
ምናልባት አሁን እንኳ በዋሻ ውስጥ ወይም በሌላ ስፍራ ተሸሽጎ ሊሆን ይችላል፤ ዳዊት በአንተ ሠራዊት ላይ አደጋ እንደ ጣለባቸው የሚሰማ ሰው ሁሉ ወዲያውኑ ወታደሮችህ እንደ ተሸነፉ አድርጎ ያወራል።
እርሱም የጦር መሣሪያ አንጋቹን ወጣት በፍጥነት በመጥራት፥ “ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ፤ ሴት ገደለችው እንድባል አልፈልግም” ሲል አዘዘው። ስለዚህ ወጣቱ በሰይፍ መትቶ ገደለው።
ዮናታንም በእጁና በጒልበቱ እየዳኸ ወደ አፋፉ ወጣ፤ ጋሻጃግሬውም ተከተለው፤ ዮናታንም በፍልስጥኤማውያን ላይ ድንገተኛ አደጋ በመጣል መታቸው፤ ጋሻጃግሬውም ገደላቸው።
በገጠር የነበሩ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ተሸበሩ፤ አደጋ ጣዮችና በሰፈር የነበሩ ወታደሮችም ሁሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እግዚአብሔር በላከባቸውም አስጨናቂ ሽብር መሬት ተንቀጠቀጠች።