1 ሳሙኤል 13:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጥረቢያ ለማሳልና የበሬ መንጃ ለማሾል የሚከፈለው ዋጋ አራት ግራም ያኽል የሚመዝን ጥሬ ብር ነበር፤ ማረሻና ዶማ ለማሾልም የሚከፈለው ዋጋ የዚሁ እጥፍ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማረሻና ዶማ ለማሾል የሚከፈለው ዋጋ ሁለት ሦስተኛ ሰቅል ሲሆን፣ መንሽና ጠገራ እንዲሁም የበሬ መንጃ ለማሾል ደግሞ አንድ ሦስተኛ ሰቅል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማረሻና ዶማ ለማሾል የሚከፈለው ዋጋ ሁለት ሦስተኛ ሰቅል ሲሆን፥ መጥረቢያ ለማሳል፥ መውጊያ ለማበጀት ደግሞ ዋጋው አንድ ሦስተኛ ሰቅል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዝመራውም ለአጨዳ ደርሶ ነበር። ለማረሻውና ለመቈፈሪያው ዋጋው ሦስት ሰቅል ነበር። መጥረቢያውንም ለማሳል፥ መውጊያውንም ለማበጀት ዋጋው ተመሳሳይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለማረሻው ጫፍና ለመቆፈሪያው ዋጋው የሰቅል ከ3 እጅ 2ቱ እጅ ነበረ። መጥረቢያውንም ለማሳል መውጊያውንም ለማበጀት ዋጋው የሰቅል ከ3 እጅ 1ዱ እጅ ነበረ። |