1 ሳሙኤል 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤል ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ ወደ ምጽጳ ጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ፊት ጠርቶ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምጽጳ ወደ ጌታ ፊት ጠርቶ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንዲሄዱ አዘዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሕዝቡን ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ጠራ። |
ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ መሪዎች ጋር ሄደ። ሕዝቡም ገዢአቸውና መሪያቸው አደረጉት፤ ዮፍታሔም በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ጉዳይ መስማማቱን ገለጠ።
ከሰሜን እስከ ደቡብ፥ ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ እንዲሁም በስተምሥራቅ በገለዓድ ምድር ያሉት የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ በአንድነትም ሆነው በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ፤
ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልጌላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት የሳኦልን ንጉሥነት አጸደቁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዓሉንም ሳኦልና መላው ሕዝብ በታላቅ ደስታ አከበሩት።