በዚያም የሚኖር አንድ ሰው “የእነዚህስ የሌሎቹ ነቢያት ሁኔታ እንዴት ነው? አባቶቻቸውስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል የምሳሌ አነጋገር የመነጨውም ከዚህ ነው።
1 ሳሙኤል 10:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ትንቢት መናገሩን ከፈጸመ በኋላ በኮረብታው ላይ ወደሚገኘው መሠዊያ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ትንቢት መናገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ትንቢት መናገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትንቢት መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ኮረብታው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትንቢት መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ኮረብታው መስገጃ መጣ። |
በዚያም የሚኖር አንድ ሰው “የእነዚህስ የሌሎቹ ነቢያት ሁኔታ እንዴት ነው? አባቶቻቸውስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል የምሳሌ አነጋገር የመነጨውም ከዚህ ነው።
የሳኦል አጐት ሳኦልንና አገልጋዩን አይቶ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ሳኦልም “አህዮች ልንፈልግ ሄደን ልናገኛቸው ስላልቻልን ሳሙኤልን ለመጠየቅ ጎራ ብለን ነበር” ሲል መለሰለት።