ያ ሰው ወይፈኑን በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆነ ካህናት ደሙን ወደ እግዚአብሔር ያቅርቡት፤ በድንኳኑ በር መግቢያ በኩል በሚገኘው መሠዊያ ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።
1 ሳሙኤል 1:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኰርማውንም ካረዱ በኋላ ሕፃኑን ወደ ዔሊ አቀረቡት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይፈኑን ካረዱ በኋላም ልጁን ወደ ዔሊ አቀረቡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይፈኑን ካረዱ በኋላም ልጁን ወደ ዔሊ አቀረቡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ፊት አቀረቡት ፤ አባቱም በየዓመቱ ለእግዚአብሔር የሚሠዋውን መሥዋዕት ሠዋ። ሕፃኑንም አቀረበው፤ ወይፈኑንም አረደ፤ እናቱም ሐና ሕፃኑን ወደ ዔሊ አገባችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይፈኑንም አረዱ፥ ሕፃኑንም ወደ ዔሊ አመጡት። |
ያ ሰው ወይፈኑን በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆነ ካህናት ደሙን ወደ እግዚአብሔር ያቅርቡት፤ በድንኳኑ በር መግቢያ በኩል በሚገኘው መሠዊያ ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።
በሕግ መሠረት፥ የመንጻት ሥርዓት የሚፈጸምበት ጊዜ ደረሰ፤ ስለዚህ ማርያምና ዮሴፍ ሕፃኑን በጌታ ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት ሄዱ።