1 ሳሙኤል 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፦ “አይደለም ጌታዬ ሆይ! እኔ በጥልቅ ሐዘን ላይ ያለሁ ሰው ነኝ፤ ወይን ጠጅም ሆነ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፤ ነገር ግን ችግሬን ለእግዚአብሔር እያቀረብኩ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፤ “ጌታዬ ሆይ፤ ሰክሬ አይደለም፤ እኔ ልቧ ክፉኛ የታወከባት ሴት ነኝ፤ ልቤን በእግዚአብሔር ፊት አፈሰስሁ እንጂ፣ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፥ “ጌታዬ ሆይ፤ አይደለም፤ እኔስ ልቧ ክፉኛ ያዘነባት ሴት ነኝ፤ የልቤን ኀዘን በጌታ ፊት አፈሰስሁ እንጂ፥ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐናም መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፤ እኔስ ወራት የባሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐናም፦ ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔስ ልብዋ ያዘነባት ሴት ነኝ፥ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፥ |
እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤ በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ ልቤ በሐዘን ይሰበራል።
ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።
እናንተ ሌሊቱን በሙሉ ተነሥታችሁ ጩኹ፤ በልባችሁ የሚሰማችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ፊት አቅርቡ፤ በየመንገዱ ማእዘን በራብ ለሚዝለፈለፉ ልጆቻችሁ ሕይወት በጸሎት እጆቻችሁን ወደ እግዚአብሔር አንሡ።
እነርሱም በአንድነት በምጽጳ ተሰበሰቡ፤ ውሃም ቀድተው ለእግዚአብሔር መባ አድርገው በማፍሰስ በዚያን ዕለት ቀኑን ሙሉ ጾሙ፤ “እኛ እግዚአብሔርን በድለናል” ብለውም ተናዘዙ፤ ሳሙኤል በእስራኤላውያን መካከል ይፈርድ የነበረው በምጽጳ ነበር።