1 ሳሙኤል 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንዲህ ሰክረሽ የምትቈዪው እስከ መቼ ነው? ይህን ስካርሽን ወዲያ አስወግጂ!” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊም “ስካሩ የማይለቅሽ እስከ መቼ ድረስ ነው? የወይን ጠጅሽን ከአንቺ አስወግጂው” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስካሩ የማይለቅሽ እስከ መቼ ድረስ ነው? የወይን ጠጅሽን ከአንቺ አስወግጂው” ሲልም ዔሊ ተናገራት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሊም አገልጋይ፦ “ስካርሽ እስከ መቼ ነው? የወይን ጠጅሽን ከአንቺ አርቂው፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ውጪ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም፦ ስካርሽ እስከ መቼ ነው? የወይን ጠጅሽን ከአንቺ አርቂው አላት። |
እንደ አረጀ ግድግዳና እንደ ተነቃነቀ አጥር ዐቅም ያነሰውን ሰው፥ ሁላችሁም በእርሱ ላይ አደጋ እየጣላችሁ። እስከ መቼ ስታጠቁት ትኖራላችሁ?