1 ጴጥሮስ 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሙታን ሳይቀር ወንጌል የተሰበከውም በዚህ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ በመንፈሳቸው ግን እግዚአብሔር በሚኖረው ዐይነት በሕይወት ይኖራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንጌል ለሙታን እንኳ ሳይቀር የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ ስለዚህ እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋ ይፈረድባቸዋል፤ በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንጌል ለሙታን ሳይቀር የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ ስለዚህ እንደ ሰው ሁሉ በሥጋ ይፈረድባቸዋል፤ በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይኖራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባችው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባችው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና። |
እነዚህ ነቢያት ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤ ያገለገሉአችሁም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት አሁን ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ ይህን ነገር መላእክት እንኳ ለማየት ይመኙት ነበር።
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።
በእሳት ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው አጠገብ ወጣና ስለታም ማጭድ የያዘውን መልአክ “የዘለላዎቹ ፍሬዎች ስለ በሰሉ ስለታም ማጭድህን ስደድ! የወይን ዘለላዎችን ሁሉ ከምድር ወይን ቈርጠህ ሰብስብ!” በማለት ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ።