1 ነገሥት 7:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚሁ መደገፊያዎችና ጠፍጣፋ ነሐሶች መካከል ባለው ክፍት ቦታ ሁሉ በኪሩቤል፥ በአንበሶችና በዘንባባ ዛፎች አምሳል በተሠሩ ቅርጾች አጊጠው ነበር፤ እንዲሁም ዙሪያቸው የአበባ ጒንጒን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በድጋፎቹና በጠፍጣፋ ናሶቹ ላይ ባለው ቦታ ሁሉ፣ ዙሪያውን የአበባ ጕንጕን እያደረገ ኪሩቤልን፣ አንበሶችንና የዘንባባ ዛፎችን ቀረጸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነዚሁ መደገፊያዎችና ጠፍጣፋ ነሐሶች መካከል ባለው ክፍት ቦታ ሁሉ በኪሩቤል፥ በአንበሶችና በዘንባባ ዛፎች አምሳል በተሠሩ ቅርጾች አጊጠው ነበር፤ እንዲሁም ዙሪያቸው የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክፈፎቻቸውም ኪሩቤልና አንበሶች የዘንባባ ዛፎችም ነበሩ፤ እያንዳንዱም ፊት ለፊት በስተውስጥና በዙሪያው ተያይዞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመያዣውና በሰንበሮቹ ላይ ኪሩቤልንና አንበሳዎችን የዘንባባውንም ዛፍ እንደ መጠናችው ቀረጸ፤ በዙሪያውም ሻኵራ አደረገ። |
ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፥ ኪሩቤልን፥ የዘንባባ ዛፎቹን፥ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው።
ልሙጥ በሆነው ነገርም ላይ በአንበሶች፥ በበሬዎችና በኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ምስሎች ነበሩ፤ ከአንበሶቹ፥ ከበሬዎቹና ከኪሩቤሉ ቅርጾች ራስጌና ግርጌ የአበባ ጒንጒን የሚመስሉ ቅርጾች ነበሩ፤
በእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ጫፍ ዙሪያ ክፈፍ ላይ ኻያ ሁለት ሳንቲ ሜትር ርዝመት ያለው አንድ ክብ ቅርጽ ነበር፤ መደገፊያዎቹና ጠፍጣፋ ነሐሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።
እንግዲህ ዐሥሩ ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎች የተሠሩት በዚህ ዐይነት ነበር። መጠናቸውና ቅርጻቸው እኩል ስለ ሆነ ሁሉም ተመሳሳይ ነበሩ።
እያንዳንዱ ኪሩብ አራት ፊቶች ነበሩት፤ የመጀመሪያው የበሬ ፊት፥ ሁለተኛው የሰው፥ ሦስተኛው የአንበሳ፥ አራተኛው ደግሞ የንስር ፊት ይመስል ነበር።
መግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ። መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።
የመግቢያው ክፍል ከውጪው አደባባይ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግድግዳ ዐምዶቹም ላይ በሁለቱም በኩል የዘንባባ ዛፍ ቅርጾች ነበሩ፤ መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።