ለሰሎሞንና በቤተ መንግሥቱ ለሚቀለቡት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብ የሚያቀርቡት ዐሥራ ሁለቱ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ወር ምንም ነገር ሳያጓድሉ በወቅቱ ያመጡ ነበር።
1 ነገሥት 4:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደአስፈላጊነቱ የሚደርስበትን ሠረገላ ለሚስቡ ፈረሶችና ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገፈራ ያቀርብ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ለሠረገላ ፈረሶችና ለፈጣን ፈረሶች የተመደበውን ገብስና ጭድ ከተፈለገው ቦታ ድረስ ያመጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደ አስፈላጊነቱ የሚደርስበትን ሠረገላ ለሚስቡ ፈረሶችና ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገፈራ ያቀርብ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዱም እንደ ደንቡ የንጉሡን ሰረገላዎች ለሚስቡ ለፈረሶችና ለሰጋር በቅሎዎች ገብስና ገለባ፥ እንዲሁም ዕቃዎችን ወደ ስፍራቸው ያመጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያንዳንዱም እንደ ደንቡ ለፈረሶቹና ለሰጋር በቅሎች ገብስና ጭድ ወደ ስፍራቸው ያመጡ ነበር። |
ለሰሎሞንና በቤተ መንግሥቱ ለሚቀለቡት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብ የሚያቀርቡት ዐሥራ ሁለቱ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ወር ምንም ነገር ሳያጓድሉ በወቅቱ ያመጡ ነበር።
መርዶክዮስ ደብዳቤዎቹን ሁሉ በንጉሥ አርጤክስስ ስም አስጽፎ የቤተ መንግሥቱን ማኅተም አተመባቸው፤ ደብዳቤዎቹም በቤተ መንግሥቱ ጋጥ በተቀለቡ ፈጣን ፈረሶች በሚጋልቡ ጋላቢዎች እጅ እንዲላኩ አደረገ።
ፈረሰኞቹም በንጉሡ ትእዛዝ በቤተ መንግሥት ፈረሶች ላይ ተቀምጠው በፍጥነት ጋለቡ፤ ይኸው ንጉሣዊ ትእዛዝ የመናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳም በይፋ ለሕዝብ እንዲነገር ተደረገ።