1 ነገሥት 17:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና እግዚአብሔርም በአንተ አማካይነት መናገሩን አሁን አረጋገጥኩ!” ስትል መለሰችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሴቲቱ ኤልያስን፣ “አሁን የእግዚአብሔር ሰው መሆንህን፣ ከአንደበትህም የወጣው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ዐወቅሁ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትዮዋም “እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና በአፍህ ያለው የጌታ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅሁ!” ስትል መለሰችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በአፍህ እውነት እንደ ሆነ አሁን ዐወቅሁ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በአፍህ እውነት እንደ ሆነ አሁን አወቅሁ፤” አለችው። |
ኤልሳዕም “በመጪው ዓመት ልክ ይህን ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርስዋም፦ “አይደለም! ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ የማይፈጸም የተስፋ ቃል አትንገረኝ!” አለችው።
ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ እኔንም አባቴንም ጠልተዋል።
አንተ ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማያስፈልግህ አሁን ዐወቅን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ወጣህ እናምናለን።”
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በቀር እነዚህን አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል ማንም የለም፤ ስለዚህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንክ እናውቃለን” አለው።
ደግሞም ስለ እናንተ ሳናቋርጥ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ምክንያት አለን፤ ይኸውም ከእኛ የሰማችሁትን የእግዚአብሔርን ቃል በተቀበላችሁ ጊዜ በእናንተ በአማኞች የሚሠራውን ይህንን ቃል የተቀበላችሁት እንደ ሰው ቃል ሳይሆን ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጋችሁ ነው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል ነው።