1 ነገሥት 17:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ በዚህም ዐይነት እርስዋ፥ ቤተሰብዋና ኤልያስም ለብዙ ቀን የሚሆን በቂ ምግብ አገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ በዚህ ሁኔታም ኤልያስ፣ መበለቲቱና ቤተ ሰቧ ብዙ ቀን ተመገቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ በዚህም ዓይነት እርሷ፥ ቤተሰብዋና ኤልያስም ለብዙ ቀን የሚሆን በቂ ምግብ አገኙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ሄዳ እንዲሁ አደረገች፤ እርስዋና እርሱ ልጆችዋም በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ሄዳ እንደ ኤልያስ ቃል አደረገች፤ እርስዋና እርሱ ቤትዋም ብዙ ቀን በሉ። |
አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም’ ሲል ተናግሮአል።”
ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታ ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቈርቈር በየማድጋዎቹ ሞላች።
ሰዎቹ በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሥተው ተቆዓ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓማ አገር ሄዱ፤ ወደዚያ ለመሄድ ጒዞ በመጀመር ላይ ሳሉም ኢዮሣፍጥ እነርሱን “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱም ብርታትን ይሰጣችኋል፤ የእግዚአብሔር ነቢያት የሚነግሩአችሁንም እመኑ፤ ይሳካላችኋልም” አላቸው።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ በሣጥኑ ውስጥ ገንዘብ ከጨመሩት ሰዎች ሁሉ አብልጣ የጨመረች ይህች ድኻ መበለት ናት።
አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእምነት ነው፤ ያ የተስፋ ቃል የተቀበለው አብርሃም አንድ ልጁን ሊሠዋው ነበር፤