1 ነገሥት 16:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መኖሪያውን በቲርጻ አድርጎ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት፣ ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ገዛ፤ ከዚህም ውስጥ ስድስቱን ዓመት የገዛው በቴርሳ ሆኖ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ዓይነት አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መኖሪያውን በቲርጻ አድርጎ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠላሳ አንደኛው ዓመተ መንግሥት ዘንበሪ በእስራኤል ላይ ዐሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴርሳም ስድስት ዓመት ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ዐሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴርሳም ስድስት ዓመት ነገሠ። |
አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ ኻያ ሁለት ዓመት ገዛ።
በነገሠም ጊዜ የኻያ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ብቻ ገዛ፤ እናቱ ዐታልያ ተብላ የምትጠራው የአክዓብ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።
አካዝያስ ዕድሜው ኻያ ሁለት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ገዛ፤ የንጉሥ አክዓብ ልጅ፥ የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ የሆነች ዐታልያ ተብላ የምትጠራ እናቱ ወደ ክፋት የሚመራ ምክር ትሰጠው ስለ ነበር አካዝያስ የንጉሥ አክዓብን መጥፎ ምሳሌነት ተከተለ፤