Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 16:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ ኻያ ሁለት ዓመት ገዛ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት፣ የዖምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፣ በሰማርያም ሆኖ እስራኤልን ሃያ ሁለት ዓመት ገዛ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ ኻያ ሁለት ዓመት ገዛ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የዘ​ን​በሪ ልጅ አክ​ዓብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ የዖምሪም ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ በሰማሪያ ኻያ ሁለት ዓመት ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 16:29
11 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ወገን በመለየት ከሁለት ተከፍለው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አንደኛው ክፍል ቲብኒ ተብሎ የሚጠራውን የጊናትን ልጅ ለማንገሥ ሲፈልግ፥ ሌላው ክፍል ደግሞ ዖምሪን ለመደገፍ ይሻ ነበር።


በዚህ ዐይነት አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መኖሪያውን በቲርጻ አድርጎ ነበር።


ከዚያም በኋላ ሼሜር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያን ኰረብታ በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛ፤ ዖምሪ ኰረብታውን ከመሸገ በኋላ ከተማ ቈረቈረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሼሜር ስም “ሰማርያ” ብሎ ሰየማት።


ዖምሪ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አክዓብ ነገሠ።


አክዓብ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የከፋ ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤


አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስል አቆመ፤ ከእርሱ በፊት ከነበሩትም የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቊጣ የሚያነሣሣ ኃጢአት ሠራ።


“ወደ ሰማርያው ንጉሥ ወደ አክዓብ ሂድ፤ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ በመውረስ ላይ እንዳለ በዚያው ታገኘዋለህ፤


በዚሁ ወቅት፥ አሜስያስ ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዲሄዱ ያልፈቀደላቸው የእስራኤል ወታደሮች በሰማርያና በቤትሖሮን መካከል በሚገኙት በይሁዳ ከተማዎች ላይ አደጋ በመጣል ሦስት ሺህ ሰዎችን ገደሉ፤ እጅግ የበዛ ምርኮም ወሰዱ።


ከሴኬም፥ ከሴሎና ከሰማርያ ሰማኒያ ሰዎች በድንገት መጡ፤ እነርሱም በሐዘን ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውን ቀደው፥ ፊታቸውን ነጭተው ነበር፤ ለቤተ መቅደስም መባ የሚያቀርቡትን እህልና ዕጣን ይዘው ነበር፤


የኤፍሬም ነገድ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ከፍ ብሎ በነበረበት ዘመን ሲናገር የሚሰሙት ሁሉ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ በኋላ ግን ባዓል ለተባለ ጣዖት በመስገድ ኃጢአት ስለ ሠራ በሞት ተቀጣ።


ይህ ሁሉ የሚደርስባችሁ የንጉሥ ዖምሪን ሥርዓት ስለ ጠበቃችሁና የንጉሥ አክዓብን አካሄድ ሁሉ ስለ ተከተላችሁ ነው፤ በእነርሱ ባህል ስለ ተመራችሁ አጠፋችኋለሁ፤ የከተማይቱን ነዋሪዎችም የሰው ሁሉ መሳቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ እንድትሸከሙ አደርጋችኋለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos