1 ነገሥት 13:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽማግሌው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ “ያ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ያልጠበቀው ነቢይ መሆን አለበት! ስለዚህም እግዚአብሔር ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል ማለት ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን ሲሰማ፣ “ይህ የእግዚአብሔርን ቃል ያቃለለው ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ቃል መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ “ይህ የጌታን ቃል ያቀለለው ያ ጌታ ሰው ነው፤ ጌታ ባስጠነቀቀው መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ያን ሰምቶ፥ “በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያመፀ ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ያን በሰማ ጊዜ “በእግዚአብሔር አፍ ላይ ያመፀ ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል፥ እግዚአብሔር ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ ሰብሮም ገድሎታል፤” አለ። |
አንዳንድ ሰዎች በዚያ በኩል ሲያልፉ አጠገቡ ከቆመው አንበሳ ጋር ሬሳው በመንገድ ላይ ተጋድሞ አዩ፤ ሽማግሌው ነቢይ ወደሚኖርበት ወደ ቤቴል ከተማ መጥተው አወሩ።
ሽማግሌ ሆነ ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃናትንና ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፤ ነገር ግን በግንባሩ ላይ ምልክት ያለበትን ማንንም አትንኩ፤ ግድያውንም ከዚሁ ከቤተ መቅደሴ ጀምሩ፤” ስለዚህ እዚያ በቤተ መቅደስ ከቆሙት መሪዎች አንሥተው ግድያውን ማካሄድ ጀመሩ።
ሙሴም አሮንን “እግዚአብሔር ‘በፊቴ ቀርቦ የሚያገለግለኝ ሁሉ ቅድስናዬን ያክብር፤ እኔም በሕዝቤ ፊት የተከበርኩ እሆናለሁ’ እያለ በተናገረበት ጊዜ ይህንኑ ማስጠንቀቁ ነበር” አለው። አሮንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ።
ፍርድ የሚጀመርበት ጊዜ ቀርቦአል፤ ፍርዱ የሚጀመረውም በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ነው፤ ታዲያ፥ ፍርድ የሚጀመረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?