1 ነገሥት 12:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኀላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህን ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሮብዓም የጕልበት ሠራተኞች አለቃ የነበረውን አዶኒራምን ላከው፤ ነገር ግን እስራኤል ሁሉ በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሡ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኀላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህን ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሮብዓም አስገባሪውን አዶኒራምን ላከ፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ደበደቡት፥ ሞተም። ንጉሡም ሮብዓም ፈጥኖ ወደ ሰረገላው ወጣ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ሸሸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሮብዓም አስገባሪውን አዶኒራምን ሰደደ፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ደበደቡት፤ ሞተም። ንጉሡም ሮብዓም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ወጣ ወደ ኢየሩሳሌምም ሸሸ። |
በእነርሱ ላይ አዶኒራም የተባለውን ሰው ኀላፊ አድርጎ ሾመ፤ ሠራተኞቹንም ዐሥር ዐሥር ሺህ አድርጎ በሦስት ቡድን በመክፈል እያንዳንዱ ቡድን ተራ ገብቶ አንድ ወር በሊባኖስ እንዲሠራ፥ ሁለት ወር ደግሞ በቤቱ እንዲያርፍ ወሰነ።
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የጒልበት ሥራ የሚሠሩ ገባሮች ኀላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህን ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ።
ንጉሥ ኢዮአስ በዘካርያስ ላይ በተደረገው ሤራ ተባባሪ ሆነ፤ ሕዝቡም በንጉሡ ትእዛዝ ዘካርያስን በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
መላውም ማኅበር በድንጋይ ወግሮ ሊገድላቸው በእነርሱ ላይ ተነሣሣ፤ ነገር ግን በመገናኛው ድንኳን የእግዚአብሔር ክብር ለእስራኤላውያን ሁሉ ተገለጠ።
ወዲያውኑ የቤተ መቅደሱ የዘበኞች አለቃና ሎሌዎቹ ሄደው አመጡአቸው፤ ያመጡአቸውም በኀይል ሳይሆን በማግባባት ነው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግራቸው በመፍራት ነው።