እስራኤላውያንም “እርሱ የእናንተ ወገን ቢሆንም እንኳ እናንተ ከምትፈልጉት ይበልጥ እኛ እንፈልገዋለን፤ ከመንግሥቱ ዐሥሩ እጅ የሚገባው ለእኛው ነው፤ እናንተ እኛን የምትንቁት ስለምንድን ነው? ንጉሡን ስለ መመለስ በመጀመሪያ ጥያቄ ያቀረብነው እኛ መሆናችንን ልትዘነጉ አይገባም!” አሉአቸው። ነገር ግን ከእስራኤል ሰዎች ይልቅ የይሁዳ ሰዎች ዳዊትን የራሳቸው ለማድረግ በብርቱ ተከራከሩ።
1 ነገሥት 11:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አኪያም የለበሰውን አዲስ መጐናጸፊያ አውልቆ ከዐሥራ ሁለት ቈራረጠው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አኪያ የለበሰውን አዲስ መጐናጸፊያ ይዞ ዐሥራ ሁለት ቦታ ቀደደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አኪያም የለበሰውን አዲስ መጐናጸፊያ አውልቆ ከዐሥራ ሁለት ቆራረጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪያም የለበሰውን አዲስ ልብስ ይዞ ከዐሥራ ሁለት ቀደደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አኪያም የለበሰውን አዲስ ልብስ ይዞ ከዐሥራ ሁለት ቆራረጠው። |