1 ነገሥት 11:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀዳድም የንጉሡ ወዳጅ ሆነ፤ ንጉሡም የሚስቱን የጣፍኔስን እኅት ለሀዳድ ዳረለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም ሃዳድን እጅግ ወደደው፤ ስለዚህም ከሚስቱ ከንግሥት ጣፍኔስ እኅት ጋራ አጋባው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀዳድም የንጉሡ ወዳጅ ሆነ፤ ንጉሡም የሚስቱን የጣፍኔስን እኅት ለሀዳድ ዳረለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዴርም በፈርዖን ፊት እጅግ ባለምዋል ሆነ። የሚስቱንም የቴቄምናስን ታላቅ እኅት ሚስት አጋባው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚስቱንም የእቴጌይቱን የቴቄምናስን እኅት እስኪያጋባው ድረስ ሃዳድ በፈርዖን ፊት እጅግ ባለምዋል ሆነ። |
ፈርዖን ለዮሴፍ “ጻፍናት ፐዕናሕ” የሚል መጠሪያ ስም አወጣለት፤ አስናት ተብላ የምትጠራውን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበር።
እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም ጥቂቶች ሰዎች ከእነርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ግብጽ ተጒዘው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም ለሀዳድ መሬትና አንድ መኖሪያ ቤት ሰጥቶ ምግብ ፈቀደለት፤
እርስዋም ገኑባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከንጉሡም ወንዶች ልጆች ጋር አብሮ ኖረ።