እርሱ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ድንገት ደረሰ፤ አዶንያስም “እስቲ ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለ ሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።
1 ነገሥት 1:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ደኅና ወሬስ ይዤ አልመጣሁም፤ ግርማዊው ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አንግሦታል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንም እንዲህ ሲል ለአዶንያስ መለሰ፣ “ነገሩ ከቶ እንዲህ አይደለም! ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አንግሦታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “በእውነት ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አነገሠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ብሎ መለሰ፥ “በእውነት ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አነገሠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ብሎ መለሰ “በእውነት ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አነገሠው። |
እርሱ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ድንገት ደረሰ፤ አዶንያስም “እስቲ ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለ ሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።
ንጉሡም እርሱን ያጅቡት ዘንድ ካህኑን ሳዶቅን፥ ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄን ልጅ በናያንና የቤተ መንግሥቱን ክብር ዘበኞች ልኮአል፤ እነርሱም ንጉሡ በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ እንዲቀመጥ አድርገውታል።