1 ነገሥት 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤርሳቤህም እንዲህ ስትል መለሰች፤ “ጌታዬ ሆይ! ልጄ ሰሎሞን የዙፋንህ ወራሽ ሆኖ እንደሚነግሥና በዙፋንህ እንደሚቀመጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም ምለህ ቃል ገብተህልኝ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም እንዲህ አለችው፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ አንተው ራስህ ለአገልጋይህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ምለህልኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም አለችው፦ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በጌታ በእግዚአብሔር ምለህልኛል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም አለችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ለአገልጋይህ፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል ብለህ በአምላክህ ምለህልኝ አልነበረምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም አለችው “ጌታዬ ሆይ! አንተ ለባሪያህ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል፤’ ብለህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ምለህልኛል፤ |
ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።
ልጅሽ ሰሎሞን በእኔ እግር ተተክቶ እንደሚነግሥ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ከዚህ በፊት የገባሁልሽን ቃል በዛሬው ዕለት የምፈጽም መሆኔን አረጋግጥልሻለሁ።”
የታዘዙትም ሣራ አብርሃምን “ጌታዬ!” እያለች ትታዘዝለት እንደ ነበረው ዐይነት ነው፤ እናንተም መልካም የሆነውን ነገር ብታደርጉና አንዳች የሚያስፈራ ነገር ባያስደነግጣችሁ የእርስዋ ልጆች ናችሁ።