1 ነገሥት 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ቤርሳቤህ ንጉሡን ለማነጋገር ወዳለበት እልፍኝ ገባች፤ ንጉሡ እጅግ ስለ ሸመገለ ሹኔማይቱ ልጃገረድ አቢሻግ በጥንቃቄ ትንከባከበው ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ቤርሳቤህ፣ ሱነማዪቱ አቢሳ በምታገለግልበት ክፍል እርጅና የተጫጫነውን ንጉሥ ለማነጋገር ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤርሳቤህም ወደ ንጉሡ እልፍኝ ገባች፥ ንጉሡም እጅግ ሸምግሎ ነበር፥ ሹኔማይቱም አቢሻግ ታገለግለው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤርሳቤህም ወደ ንጉሡ ወደ እልፍኝ ገባች፤ ንጉሡም እጅግ ሸምግሎ ነበር፤ ሱነማዪቱም አቢሳ ንጉሡን ታገለግለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤርሳቤህም ወደ ንጉሡ ወደ እልፍኝ ገባች፤ ንጉሡም እጅግ ሸምግሎ ነበር፤ ሱነማይቱም አቢሳ ታገለግለው ነበር። |
አንዲት ቈንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፍለጋ ተደረገ፤ ሹኔም ተብላ ከምትጠራው ስፍራ አቢሻግ የምትባል አንዲት ልጃገረድ አግኝተው ለንጉሡ አመጡለት፤