1 ዮሐንስ 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን መንፈስ ለይታችሁ የምታውቁት በዚህ ነው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የሚያምን መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚያምን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ |
ስለዚህ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ ኢየሱስን የሚረግም ማንም የለም፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው!” የሚል ማንም እንደሌለ እነግራችኋለሁ።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።
ይህ ሕይወት ተገልጦአል፤ እኛም አይተነዋል፤ እንመሰክራለንም። በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለም ሕይወት እንነግራችኋለን።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የማያምን መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም፤ ይህም መንፈስ ይመጣል ሲባል የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው፤ እርሱ አሁን እንኳ በዓለም ላይ አለ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የማያምኑ ብዙ አሳሳቾች በዓለም ተነሥተዋል። እንዲህ ያለው ሰው አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።