1 ዮሐንስ 4:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አስቀድሞ ስላፈቀረን እኛም እናፈቅራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና እኛ እንወድደዋለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ አስቀድሞ ስለወደደን፥ እንወዳለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። |
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
ፍቅር ማለት እንዲህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደንና ኃጢአታችንን እንዲደመስስ ልጁን ስለ ላከልን ነው።