1 ዮሐንስ 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆች ሆይ! ማንም አያታላችሁ፤ ክርስቶስ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ጻድቅ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆች ሆይ፤ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፥ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው። |
አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ታውቁ የለምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖት አምላኪዎች፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
አብርሃምም ከያዘው ነገር ሁሉ ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው፤ የመልከ ጼዴቅ የስሙ ትርጓሜ አንደኛው “የጽድቅ ንጉሥ” ሌላው “የሳሌም ንጉሥ” ወይም “የሰላም ንጉሥ” ማለት ነው።
ልጆቼ ሆይ! ይህን የምጽፍላችሁ ኃጢአት እንዳትሠሩ ብዬ ነው። ነገር ግን ማንም ሰው ኃጢአት ቢሠራ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በዚህ ዓለም እኛ የምንኖረው ልክ ክርስቶስ እንደሚኖረው እንደ መሆኑ ፍቅራችን ፍጹም ቢሆን በፍርድ ቀን ያለ ፍርሀት በፊቱ ለመቅረብ ሙሉ መተማመን ይኖረናል።