እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
1 ዮሐንስ 1:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስታችን ሙሉ እንዲሆን ይህን እንጽፍላችኋለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የምንጽፍላችሁ ደስታችን እንዲፈጸም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስታችን ሙሉ እንዲሆን ይህን እንጽፍላችኋለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን። |
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
ሙሽሪት ያለችው ሰው ሙሽራ ነው፤ የሙሽራው ሚዜ ግን ከሙሽራው አጠገብ ቆሞ ይሰማዋል፤ የእርሱንም ድምፅ በመስማት ይደሰታል፤ ስለዚህ የእኔም ደስታ ይህ ነው፤ እርሱም አሁን ፍጹም ሆኖአል።
ልጆቼ ሆይ! ይህን የምጽፍላችሁ ኃጢአት እንዳትሠሩ ብዬ ነው። ነገር ግን ማንም ሰው ኃጢአት ቢሠራ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ልጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበረኝ፤ ነገር ግን ሁሉንም በደብዳቤ ልገልጸው አልፈልግም፤ ይልቅስ ደስታችን ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ቃል በቃል ላነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።