La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 7:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ባለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደ ገና ዐብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለጸ​ሎት እን​ድ​ት​ተጉ ከም​ት​ስ​ማ​ሙ​በት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አት​ለ​ያዩ፤ ዳግ​መኛ ሰይ​ጣን ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጋ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት ኑሩ፤ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ደካማ ነውና ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 7:5
11 Referencias Cruzadas  

ሙሴም ሰዎቹን “ለተነገወዲያው ዕለት ተዘጋጁ፤ እስከዚያም ቀን ድረስ ወደ ሴት አትቅረቡ” አላቸው።


ሁለተኛ ሚስት ቢያገባ ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግብና ልብስ መስጠቱን አይተው፤ ቀድሞ የነበራትንም የጋብቻ መብት አይከልክላት።


ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስባችሁ፥ ለተቀደሰ ጉባኤ አዘጋጁ፤ ሽማግሌዎችን ጥሩ፤ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን ጭምር ሰብስቡ፤ ሙሽራዎችም ሳይቀሩ ከጫጒላቸው ይውጡ።


የቤተ መቅደሱን ካህናትና ነቢያትን “እስከ አሁን ለብዙ ዓመቶች እንዳደረግነው በየአምስተኛው ወር በመጾም ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ ማዘናችንን እንቀጥልን?” ብለው እንዲጠይቁ ነበር።


እንዲህ ዐይነቱ ጋኔን ግን በጸሎትና በጾም ካልሆነ በቀር ከቶ አይወጣም።”


ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ልዩ ችሎታ ለተሰጣቸው ነው እንጂ ይህ ነገር ለሁሉም አይሆንም።


የዚያን ጊዜ ኢየሱስ “ ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ!’ ተብሎ ተጽፎአልና ወግድ አንተ ሰይጣን!” አለው።


ሚስት በሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ በእርስዋ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያለው ባልዋ ነው። እንዲሁም ባል በሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ በእርሱ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ነች።


በዚህ ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ በትዕግሥት መጠበቅ ባለመቻሌ ስለ እምነታችሁ ማወቅ ፈልጌ ጢሞቴዎስን ወደ እናንተ ላክሁት፤ እርሱን የላክሁትም ምናልባት ፈታኙ በአንድ መንገድ ፈትኖአችሁ ይሆናል፤ ሥራችንም ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል በማለት ፈርቼ ነው።