1 ቆሮንቶስ 3:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሁሉ ነገር የእናንተ ስለ ሆነ ማንም በሰው አይመካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ማንም በሰው አይመካ። ሁሉ ነገር የእናንተ ነውና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም፥ ሁሉ ነገር የእናንተ ነውና፥ ማንም በሰው አይመካ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እንግዲህ አንዱ ስንኳ በሰው አይመካ፤ ሁሉ የእናንተ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ |
ወንድሞች ሆይ! እናንተን ለመጥቀም ብዬ በዚህ ጉዳይ እኔንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ አድርጌ ተናገርኩ፤ ይህንንም ያደረግኹት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ምክር ትርጒሙን ከእኛ እንድትማሩ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በአንድ ሰው መመካት ሌላውን ሰው ግን መናቅ አይገባችሁም።
እኛ የምናስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ራሳችን ስለ ኢየሱስ የእናንተ አገልጋዮች መሆናችንን ነው እንጂ ስለ ራሳችንስ አንሰብክም።