ይሰሙን ከነበሩትም ሴቶች አንድዋ የትያጥሮን ከተማ ተወላጅ የሆነች የቀይ ልብስ ነጋዴ፥ ልድያ የምትባል ሴት ነበረች፤ እርስዋ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሴት ነበረች፤ ጌታም ልቡናዋን ስለ ከፈተላት ጳውሎስ የሚናገረውን ቃል ታዳምጥ ነበር፤
1 ቆሮንቶስ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረግኹት እምነታችሁ በሰው ጥበብ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በእግዚአብሔር ኀይል የተደገፈ እንዲሆን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኀይል እንጂ በሰው ጥበብ ላይ እንዳይመሠረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰዎች ጥበብ እንዳይሆን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማመናችሁ በእግዚአብሔር ኀይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን። |
ይሰሙን ከነበሩትም ሴቶች አንድዋ የትያጥሮን ከተማ ተወላጅ የሆነች የቀይ ልብስ ነጋዴ፥ ልድያ የምትባል ሴት ነበረች፤ እርስዋ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሴት ነበረች፤ ጌታም ልቡናዋን ስለ ከፈተላት ጳውሎስ የሚናገረውን ቃል ታዳምጥ ነበር፤
ክርስቶስ የላከኝ የወንጌልን ቃል እንዳስተምር ነው እንጂ እንዳጠምቅ አይደለም፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር የወንጌልን ቃል የማስተምረው ከሰው ጥበብ በተገኘ ንግግር አይደለም።
ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።
ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።