እንዲሁም ንጉሥ ሆይ! ንጉሥ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነና መልካሙን ከክፉው ለይቶ ስለሚያውቅ የተስፋ ቃልህ በሰላም እንድኖር ይረዳኛል ብዬ አስቤ ነው እንግዲህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን!”
1 ቆሮንቶስ 2:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለው ግን ሁሉን ነገር መመርመር ይችላል፤ እርሱ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉንም ነገር ይመረምራል፤ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል፤ እሱ ግን በማንም አይመረመርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል፤ እርሱን ግን የሚመረምረው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። |
እንዲሁም ንጉሥ ሆይ! ንጉሥ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነና መልካሙን ከክፉው ለይቶ ስለሚያውቅ የተስፋ ቃልህ በሰላም እንድኖር ይረዳኛል ብዬ አስቤ ነው እንግዲህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን!”
ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይዞ መሄድ ስለ ፈለገ በዚያ ስፍራ በነበሩት አይሁድ ምክንያት እንዲገረዝ አደረገው፤ ይህንንም ያደረገው እነርሱ የጢሞቴዎስ አባት አረማዊ መሆኑን ያውቁ ስለ ነበረ ስለ እነርሱ ብሎ ነው።
ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ሳስተምራችሁ ሥጋውያንና በክርስቶስ ገና ያልጠነከራችሁ ሕፃናት እንደ መሆናችሁ መጠን ነው እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ መጠን አይደለም።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
ወንድሞች ሆይ! ሰው ተሳስቶ አንዳች ጥፋት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዐይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት፤ ነገር ግን አንተም በዚህ ዐይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።
ስለዚህ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እናንተ በመንፈሳዊ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምትገነዘቡበት ሙሉ ዕውቀት እንዲኖራችሁ ለእናንተ ከመጸለይና እግዚአብሔርን ከመለመን አላቋረጥንም።
ወዳጆች ሆይ! በዓለም ላይ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ስለ ተነሡ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ይልቅስ መንፈሶች የእግዚአብሔር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን መርምሩ።