በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”
1 ቆሮንቶስ 15:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሰማያዊ አካል አለ፤ ምድራዊ አካልም አለ፤ ነገር ግን የሰማያዊው አካል ክብር አንድ ዐይነት ነው፤ የምድራዊውም አካል ክብር ሌላ ዐይነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሰማያውያን አካላት አሉ፤ ምድራውያን አካላት አሉ፤ ነገር ግን የሰማያዊ አካላት ክብር አንድ ነው፤ የምድራዊም አካላት ክብር ሌላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሰማያውያን አካሎች አሉ፤ ምድራውያን አካሎች አሉ፤ ነገር ግን የሰማያዊ አካሎች ክብር አንድ ነው፤ የምድራዊም አካሎች ክብር ሌላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያዊ አካል አለ፤ ምድራዊ አካልም አለ፤ ነገር ግን በሰማይ ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው፤ በምድርም ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ሰማያዊ አካል አለ፥ ምድራዊም አካል አለ፤ ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር ልዩ ነው። የምድራዊም አካል ክብር ልዩ ነው። |
በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”
ሥጋ ሁሉ አንድ ዐይነት አይደለም፤ የሰው ሥጋም አንድ ዐይነት ነው፤ የእንስሳ ሥጋ ሌላ ዐይነት ነው፤ የወፎች ሥጋ ሌላ ዐይነት ነው፤ የዓሣ ሥጋ ሌላ ዐይነት ነው።
የፀሐይ ክብር አንድ ዐይነት ነው፤ የጨረቃ ክብር ሌላ ዐይነት ነው፤ የከዋክብትም ክብር ሌላ ዐይነት ነው፤ አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ የተለየ ክብር አለው።