1 ቆሮንቶስ 15:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ሰው አስተሳሰብ እኔ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ጥቅሜ ምንድን ነው? ሙታን ከሞት የማይነሡ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት ኑ እንብላ፤ እንጠጣ” እንደ ተባለው መሆኑ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኤፌሶን ከአራዊት ጋራ የታገልሁት ለሰብኣዊ ተስፋ ብቻ ከሆነ ትርፌ ምንድን ነው? ሙታን የማይነሡ ከሆነ፣ “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ፤” እንደሚሉት መሆናችን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሰው አስተሳሰብ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ምን ሊፈይድልኝ ነው? ሙታን የማይነሡ ከሆነ፤ ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ በኤፌሶን ከአውሬ ጋር የታገልሁ ለሰው ብዬ ነውን? ምንስ ይጠቅመኛል? ሙታን የማይነሡ ከሆነ እንግዲህ እንብላ እንጠጣ፥ ነገም እንሞታለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። |
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
እንግዲህ ለሰው የሚጠቅመው ነገር ቢኖር፥ ደክሞ በመሥራት ያፈራውን ሁሉ በመብላትና በመጠጣት ራሱን ለማስደሰት መቻሉ ነው፤ ይህም ከእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን ተረድቼአለሁ።
እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ።
ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።
ነገር ግን የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያሳይ ከሆነ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን ቢቀጣን ትክክለኛ ፈራጅ አይደለም ማለት ነውን? እዚህ ላይ የምናገረው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነው።
እኔ እንዲህ ለሰው በሚገባ ቋንቋ የምናገረው ከአስተሳሰባችሁ ደካማነት የተነሣ ነው። አስቀድሞ የሰውነት ክፍሎቻችሁን የርኲሰትና የዐመፅ አገልጋዮች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ ሁሉ እንዲሁም አሁን የሰውነት ክፍሎቻችሁ እንዲቀደሱ የጽድቅ አገልጋዮች አድርጋችሁ አቅርቡ።
ወንድሞቼ ሆይ! እስቲ ይህን ነገር በሰው ዘንድ ከተለመደ ነገር ጋር አነጻጽሩት፤ አንድ ሰው የገባው ቃል ኪዳን እንኳ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሰው ሊሽረው ወይም ሊጨምርበት አይችልም።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ይሳደባሉ፤ እነርሱ ለመጠመድና ለመገደል እንደ ተወለዱ፥ በተፈጥሮ ስሜት እንደሚኖሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች ናቸው፤ እንስሶች እንደሚጠፉ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።
እነዚህ ሰዎች ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ሁሉ ይሳደባሉ፤ አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች በተፈጥሮ ስሜት የሚያውቁት ነገር ቢኖር እንኳ በእርሱ ይጠፋሉ።