Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 73:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሐሳቤን በቅንነት መጠበቄና በደልንም ከመሥራት መቈጠቤ ምን ጠቀመኝ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አንተ ባሕ​ርን በኀ​ይ​ልህ አጸ​ና​ሃት፤ አንተ የእ​ባ​ቡን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበ​ርህ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 73:13
12 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ንጹሕነቴን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤ መሠዊያህንም በመዞር አንተን አመልካለሁ።


‘እግዚአብሔርን ማስደሰት፥ ለሰው ምንም አይጠቅመውም’ ይላል።


‘እናመልከው ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ማነው? ወደ እርሱስ መጸለይ ምን ይጠቅመናል?’ ይላሉ።


‘ኃጢአት ባልሠራ ምን እጠቀማለሁ? ምንስ አተርፋለሁ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል፤ እናንተ ኃጢአተኞች! እጆቻችሁን አጽዱ፤ እናንተ ወላዋዮች! ልባችሁን አጥሩ።


እናንተ ‘እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዞቹን መጠበቅና እንደ ሐዘንተኞች በሠራዊት አምላክ ፊት መመላለስ ምን ይጠቅመናል?


አምላክ ሆይ! ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፤ አዲስና የጸና መንፈስን ስጠኝ።


ይህን ማድረግ የሚችል፥ እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥ ጣዖትን የማያመልክ፥ ዋሽቶ የማይምል ነው።


ይህም ሁሉ ሆኖ አንተ ወደ አዘቅት ትጥለኛለህ፤ የገዛ ልብሴ እንኳ ይጸየፈኛል።


ሮሮዬን ልርሳ፥ ፊቴንም ማጥቈር ትቼ ፈገግታ ላሳይ ብል፥


እንግዲህ በደለኛ ሆኜ ከተቈጠርኩ፥ በከንቱ መድከሜ ለምንድን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios