La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 11:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምታደርጉት ክፉ እንጂ መልካም ነገር ስላልሆነ በዚህ አሁን በምሰጣችሁ ትምህርት አላመሰግናችሁም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚጐዳ እንጂ ለሚጠቅም ስላልሆነ፣ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ እያመሰገንኋችሁ አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ይህን ትእዛዝ ስሰጥ አላመሰግናችሁም፤ ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚሻል ሳይሆን ለሚከፋ በመሆኑ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ላመ​ሰ​ግ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ ወደ ዝቅ​ተኛ እንጂ ወደ​ሚ​ሻል ግብር አት​ሄ​ዱ​ምና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚከፋ እንጂ ለሚሻል ስላልሆነ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ የማመሰግናችሁ አይደለም።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 11:17
14 Referencias Cruzadas  

በግልጽ የሚነገር ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።


“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው።


ገዢዎች የሚያስፈሩት ክፉ አድራጊዎችን እንጂ መልካም አድራጊዎችን አይደለም፤ ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ መልካሙን ነገር አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ።


ዘወትር ስለምታስታውሱኝና የሰጠኋችሁንም ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ፥ አመሰግናችኋለሁ።


በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምትበሉት የጌታን ራት አይደለም።


ኧረ ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትንቃላችሁን? ወይስ ምንም የሌላቸውን ችግረኞች ታሳፍራላችሁን? እንግዲህ ምን ልበላችሁ? ስለዚህ ነገር ላመስግናችሁን? ከቶ አላመሰግናችሁም!


መሰብሰባችሁ ለፍርድ እንዳይሆን ከመካከላችሁ የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር እኔ እዚያ ስመጣ ተጨማሪ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።


ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች ቢናገርና የማያውቁ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢመጡ ተናጋሪዎችን “እነዚህ ሰዎች አብደዋል” አይሉምን?


ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት።


ዘወትር እየተገናኘን እርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።


ለአገረ ገዢዎችም ታዘዙ፤ እነርሱ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት፥ መልካም አድራጊዎችን ለማመስገን ከንጉሠ ነገሥቱ የሚላኩ ናቸው።